የኢትዮጵያ ኮንስትራሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ የሲቪል መሀንዲሶች ማህበር በጋራ ለመሥራት የሚስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ኮንስትራሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ የሲቪል መሀንዲሶች ማህበር በጋራ ለመሥራት የሚስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ህዳር 15 ቀን 2012 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ እንደተገለጸው ማህበሩ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመው በተለያዩ የሲቪል ምህንድስና ሥራዎች ዙሪያ አብሮ ለመሥራት ፍላጎት ስላለው ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ፕሬዚዳንት ኢንጅነር ተስፋዬ ወርቅነህ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኮንስትራሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የማህበሩ አባል መሆኑ በበርካታ ሥራዎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ትልቅ አቅም ይፈጥራል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የሀገሪቱ የመንግስት አንጋፋ የኮንስትራክሽን ድርጅት በመሆኑ ከሀገር ውጪ የሚተርፍ አቅም አለው ያሉት ኢንጅነር ተስፋዬ ስምምነቱ በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን መሀንዲሶች የማህበሩ አባል በማድረግ የዓላማው ደጋፊ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡
የማህበሩ አባል መሆን መሀንዲሶቹ የሙያ አጋዥ ከመሆናቸው በተጨማሪ በስልጠና፣ በምርምርና ስርጸት እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጆዎችን እና አሠራሮችን በጋራ ለመካፈል ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው የሙያ ማህበራትን አቅም መጠቀም ለኮርፖሬሽኑ ትልቅ ድጋፍ እንደሚሆን ጠቅሰው ከዚህ ስምምነት ጀምሮ ከኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር ጋር ተከታታይ ግንኙነት መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ከሙያ ማህበራት ጋር አብሮ መሥራት በሲቪል ሥራዎች ዙሪያ ለሚገጥሙ ችግሮች መፍትሄ ለመፈለግ እንደሚያስችል ኢንጅነር ዮናስ ገልጸዋል፡፡
በቅርቡ ማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤውን ስለሚካሂድ ኮርፖሬሽኑ በጉባዔው ላይ እንዲሳተፍ ኢንጅነር ተስፋዬ ጥሪ አቅርበዋል፡፡