ማህበሩ ለ12 አንጋፋ አባላቱ እውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ ሲቪል መሓንዲሶች ማህበር ላለፉት በርካታ አመታት በማህበሩ አባልነት፣ የሥራ መሪነት እና በተለያዩ የመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት አመራርነት በማገልገል፣ ለኮንስትራክሽ ኢንዱስትሪው እና ለአገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለአበረከቱ ለ12 አባቱ እውቅና ሰጠ፡፡

ማህበሩ ለአንጋፋ አባላቱ የምስጋና እና የዕውቅና ሽልማት የሰጠው የማህበሩ 23ኛ አመት ጠቅላላ ጉባዔውን ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም “ስነምግባር የተላበሰ ሙያዊ አገልግሎት ለህዝባችን እና ለአገራችን ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በእንጦጦ ፓርክ አርት ጋላሪ እና ኦላይን ባከናወነበት ወቅት ነው፡፡

የማህበሩ ፕሬዚደንት የሆኑት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በእውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት በዕለቱ የዕውቅና የተሰጣቸው የማህበሩ አባላት የአገራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪእድገት አሁል ለደረሰበት ደረጃ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ፣ በተሰማሩበት የሲቪል ምህንድስና ሙያ በርካታ ጥናትና ምርሮችን ያደረጉ፣ ማህበሩ ጠንካራ ማህበር እንዲሆን በአባልነት እና በአመራርነት የሰሩ ናቸው፡፡

ይህ አይነት የእውቅና መስጠት ስርዓት ቀደም ባሉት አመታት እንዳልነበረ፣ ይህ አይነት የእውቅና እና የምስጋና ስነስርዓት መጀመሩ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ሙያተኞች ከማመስገን ባለፈ በምህንድስና ሙያ ዘርፍ ተተኩ ሙያተኞችን ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ፕሬዘደንቱ ተናግረዋል፡፡

የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሲቪል መሓንዲሶች ማህበር ላለፉት ከ50 በላይ አመታት በርካታ ውጣውረዶችን በማሳለፍ ዛሬ ላይ መድረሱን፣ ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለደረሰበት ደረጃ ደግሞ ዛሬ እውቅና የተሰጣቸውን የምህንድስና ባለሙያዎች ጨምሮ ሌሎች አባላት የነበራቸው ድርሻ ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በዕለቱ በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው የሲቪል ምህንድስና ሙያ ዘርፎች በሆኑት በኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማኔጅመንት፣ ስትራክቸራል ኢንጂነሪንግ፣ ሃይድሮሊክስ ነደ ዋተር ሪሶርስ ማኔጅመንት፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ዘርፍ እና ሮደ ኤንድ ሃይዌይ ኢንጂነርንግ ዘርፎች በማስተማር፣ ጥናትና ምርምር በማድረግ እንዲሁም በኮንስትራክሽን ዘርፉ በመሳተፍ እንዲሁም በሙያ ማህበሩ መስራች አባል በመሆን ማህበሩን በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው እና በገነዘባቸው ባበረከቱት አስተዋጽኦ የተመረጡት ተሸላሚዎች የተዘጋጀላቸውን የሰርተፊኬትና ዋንጫ ሽልማት ከማህበሩ ፕሬዚደንት ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እጅ ተቀብለዋል፡፡ እውቅና ከተሰጣቸው 12 ተሸላሚዎች መካከል ሁለቱ በህይወት እንደሌሉ በጠቅላላ ጉባዔው ላይ ተገልጧል፡፡

ማህበሩ እውቅና የተሰጣቸው ተሸላሚዎች ከታች የተጠቀሱት ናቸው፡፡ እነሱም፡-

ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራ፡-

ኢንጂነር ሃይሌ አሰግዴ

ፕሮፌሰር አበበ ድንቁ

ኢንጂነር ፈቃዴ ሃይሌ

ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ

ዶክተር ባዩ ጫኔ

ዶክተር ሚኪያስ አባይነህ

ዶክተር ሽፈራው ታየ

ዶክተር መሰለ ሃይሌ

ኢንጂነር ተስፋሚካዔል ናሁሰናይ

ፕሮፌሰር ንጉሴ ተበጀ (በህይወት የሌሉ) እና

ኢንጂነር ታደሰ ሃይለስላሴ (በህይወት የሌሉ) ናቸው፡፡