የማህበሩ የቀድሞ ፕሬዚደንትና አዲሱ ፕሬዚደንት የርክክብ ስነ ስርዓት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ሲቪል መሀንዲሶች ማህበር የቀድሞ ፕሬዚደንት ኢንጂነር ተስፋየ ወርቅነህና አዲሱ ፕሬዚደንት ኢንጂነር ዮናስ አያሌው እንዲሁም የስራ አስፈፃሚና የተለያዩ ኮሚቴዎች የርክክብ ስነ ስርዓት በቀን 21/06/12 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ ከርክክብ ስነ ስርዓቱ በተጨማሪ የታደሰው የማህበሩ ቢሮ ምርቃት፣ ማህበሩን ለሁለት አመታት ሲመራ የነበረው የቀድሞው ስራ አስፈፃሚ የሰራቸው ስራዎች ሪፓርት፣ የአዲሱ ፕሬዚደንት የስራ መጀመሪያ ንግግርና ለማህበሩ በተለያየ ደረጃ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

የማህበሩ ቢሮ ከደርባ ሲሚንቶ፣ ከኢንጂነር ሀይሌ አሰግዴ፣ ከ ኤም ኤች ኢንጂነሪንግና ሌሎች አባላት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በኢንጂነር ተስፋየ ወርቅነህ፣ ኢንጂነር ብሩክ አንተነህ፣ ኢንጂነር አማኑኤል መኮነን፣ ኢንጂነር ሰይፉ ቢሆነኝ፣  ኢንጂነር ሺፈራው አለሙ፣ ዶክተር ሚኪያስ አባይነህና  ዶክተር ካሳሁን አድማሱ አስተባባሪነት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በእለቱም ቢሮው በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አለማየሁ ተፈራና ምክትል ሰብሳቢ ኢንጂነር አበበ በለጠ ተመርቋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የማህበሩ የቀድሞ ፕሬዚደንት የነበሩት ኢነጂነር ተስፋየ ወርቅነህ በቀድሞው አመራር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን በንግግራቸውም ‹‹የኢትዮጵያ 2050›› መርሀ ግብር ዝግጅት ላይ ማህበሩ የነበረውን የመሪነት ሚና ጨምሮ በማህበሩ የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎችን አቅርበዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ በነበረው ውይይትም ነባሩ አመራር ለሰራቸው ስራዎች ከተሳታፊ አባላት አድናቆት ተበርክቶለታል፡፡ በተጨማሪም በማህበሩ የሚዲያ (IT) ስራዎች ዙሪያ አጭር ሪፖርት ቀርቧል፡፡

ቀጥሎ በተካሄደው የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ማህበሩን ለ 20 አመታት በቋሚ ሰራተኛነት በቅንነት ሲያገለግሉ ለቆዩትና እያገለገሉ ላሉት ለወ/ሮ አለም እና ሌሎች የማህበሩን ቢሮ በማሳደስና ሌሎች ስራዎች አስተዋፅኦ ላበረከቱ አባላት የምስጋና ምስክር ወረቀትና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በመቀጠልም አዲሱ የማህበሩ ፕሬዚደንት ንግግር ያደረጉ ሲሆን በሲቪል ምህንድስና ሙያ ላይ የማህበሩን ሚና ስለማሳደግና ሌሎች ወደፊት ሊሰራባቸው ስለሚገባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች አንስተዋል፡፡ በመጨረሻም መርሀ ግብሩ የቀድሞውን ፕሬዚደንት በመሸኘትና የጋራ ፎቶ በመነሳት ተጠናቋል፡፡