ጋዜጣዊ መግለጫ
ከአገር ውጭና አገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የአገራችንን የወደፊት ዘርፈ ብዙ የዕድገትና የልማት፣ የውሃ ሃብትና የምግብ ዋስትና፣ የጤናና ግዙፍ የከተሞች ግንባታ፣ ቀጣይነት ያለውና ለአየር ንብረት ለውጥ ራሱን ያዘጋጀ ኢኮኖሚ፣ የመጓጓዣና የመገናኛ አውታሮች፣ የትምህርት፣ የኃይል አቅርቦት፣ ዘመናዊ የፋብሪካ ክንዋኔዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ዘዴዎች ልማትና ማስፋፊያ ተግባራት፣ አጠቃላይ የመጪ ዘመናትና የመሠረተ ልማት አቅርቦቶችን አስመልክቶ አገራችን የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ሊኖራት ይችላል ተብሎ የሚገመተውን ወደ 200 ሚሊዮን የሚጠጋ የህዝብ ብዛት መሠረት ባደረገ ሁኔታ ከመከሩ በኋላ፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችና አገሪቷ ያላትን ታላቅ የሰውና ሌሎች ሃብቶችን መሠረት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ይቻል ዘንድ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ የተለያዩ አገራዊ ፍላጎቶችን ለማርካት በሚቻልበት ሂደት ላይ ለመምከር፣ አዲስ አበባ ላይ ታህሳስ 9 እና 10, 2012 ዓ.ም ፣የሚካሄድ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ተዘጋጅቷል። የጉባዔውን አጠቃላይ ይዘትና ተያያዥ ጉዳዮችን ቀደም ሲል ለጉባዔው በተዘጋጀው የመረጃ መረብ http//www.ethiopia2050.com ላይ ማየት ይቻላል።
ይኸው ታላቅ አገራዊ አጀንዳ አገራዊ መሠረት እንዲኖረውና ቀጣይ እንቅስቃሴዎች ሁሉ በአገር ውስጥ ድርጅታዊና ህጋዊ መሠረት በሚኖረው ሁኔታ እንዲቀጥል ለማድረግ ታስቦ፣ ይህንኑ ጽኑ መሠረት ላይ ለማስቀመጥ በማሰብ ጠንካራና ዓብይ ድርሻ እንዳላቸው የሚታሰቡ ተቋማትና አገር በቀል ማህበራት አመራሩን እንዲይዙ በማሰብ፣ አራት አካላት ለዚሁ ተግባር በተመረጡትና ይልቁንም የዓላማው ደጋፊ በመሆናቸው ታላቅ ድርሻና ሚና እንደሚኖራቸው፣ እንዲሁም ይህንን ጅምር ዘለቄታ ባለው መልክ ዘመናትን እንደሚያሻግሩት የታመነባቸው የኢትዮጵያ የምህንድስና ሙያ ማህበራት ጥምረት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር እና ዩኒቲ ዩኒሸርስቲ እንዲሁም በተባባሪ አዘጋጅነት የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር በጋራ-አስተናጋጅነት እንዲያካሄዱት ተደርጓል።
አዘጋጅ ተቋማቱ የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት እድገቱ እንደሚቀጥልና እ.ኢ.አ በ2050 የህዝብ ቁጥር ሁለት መቶ ሚሊዮን እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም የፓሊስ ፕላንና እርምጃዎች አስቀድመው በተግባር ላይ የማይውሉ ከሆነ በዚህ ምክንያት በቂ የምግብ ዋስትና፣ የሀይል፣ የመኖሪያ ቤት፣ የመጓጓዣ እና የህክምና አገልግሎቱ ለህብረተሰቡ በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ አስቸጋሪ እንደሚሆንና የህብረተሰቡን ኑሮ ከፍተኛ የሆነ ስጋት ይዞ የሚመጣ ይሆናል፡፡
እነዚህ አስፈላጊ ሁኔታዎች አስቀድመው የቅድመ ሁኔታ ጥረቶች ካልተደረጉና ቅድመ ዝግጅት እቅድ ካልተዘጋጀላቸው ድህነቱን ለማጥፋት የሚከብድ ባቻ ሳይሆን የማህበረሰቡ ችግር ለማስወገድ በጣም አስቸጋሪ በሆነው ሁኔታ እንደሚደርስ ምሁራንና አዘጋጅ ተቋማቱ ይስማሙበታል፡፡
የጋራ አስተናጋጅ ተቋማቱና የስብሰባውን ዓላማና በውስጡ የተካተቱ ጉዳዮችን በአንክሮ በማየትና በማጥናት፣ በአብዛኛውም በየግላቸው በሚያካሄዷቸው ጥናቶችና የህዝባችን ቁጥር እያደገ በሚሄድበት ወቅት ተገቢውና በምርምር ላይ የተመሠረተ ዝግጅት በማድረግ ዕድገቱ ወደትሩፋት የሚቀየርበት፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ ሊያስከትል የሚችለው አገራዊ ዕንቅፋት አሳሳቢ....