Telegram Facebook

Announcement

የበጎ ፍቃደኝነት ጥሪ - CALL FOR VOLUNTEER

February 7, 2022

የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር በአገራችን በተከሰተው ጦርነት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በተሻለ ሁኔታ ዳግም እንዲገነቡ የሞያዊ ድጋፍ ለማድረግ እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከዚህም አንዱ አካል የሆነው የትምህርት ቤቶች እድሳት (3000 ት/ቤት) እና ዳግም ግንባታ(1100 ት/ቤት) ለማከናወን ከትምህርት ሚኒስትር ጋር በመስራት ላይ ይገኛል።

ስለዚህም ከማህበሩ ጋር በበጎ ፍቃደኝነት መስራት የምትፈልጉ የማህበሩ አባላት፣ ድርጅቶች እና የአላማው ደጋፊዎች ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የፍላጎት መግለጫውን በመሙላት እንድትመዘገቡ ማህበሩ ጥሪ ያሰተላልፋል።

ማህበሩ የለያቸው ስራዎች

  • የቅድመ ጥናት ስራዎች ( Assessment/ site Reconnaissance, feasibility study, Geotechnical investigation…)
  • ዲዛይን ስራዎች (Structural design, Sanitary and other engineering designs)
  • በጥናቶች መሰረት የግንባታ መፍትሄ ማዘጋጀት(Remedial Measures and construction methodologies… )
  • የሰነድ ዝግጅቶች (Preparation of Bill of quantities, Cost Estimation detailed specification, cost estimation and contract documents)
  • የክትትል እና ጥራት ቁጥጥር  (The supervision & quality assurance)
  • ፕሮጀክት ማኔጀመንት (project management)
  • ሌሎች ድጋፎች____________________

በተጨማሪ ሁሉም ተመዝጋቢ የሚከተሉትን መረጃዎች በኢሜል eacetraining@gmail.com subject label “Volunteer” በሚል እስከ የካቲት 07 2014 መላክ አለባቹሁ። ሁሉም ከጀማሪ እስከ ከፍተኛ ባለሞያ/ድርጅት የሚያሳትፍ ስለሆነ ማህበሩ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ ያስተላልፋል።

መመዝገቢያ ማስፈንጠሪያ፡  https://forms.gle/QdVqejok6QoGNfdHA

ግለስብ

መታውቂያ (አባል ላልሆኑ)፣ የስራ ልምድ (ለሁሉም ፣ካለ) እና የትምህርት መስረጃ (አባል ላልሆኑ)

በድርጅት

ንግድ ፍቃድ፣ ቲን፣ የስራ ልምድ (ካለ) እና ብቃት ማረጋገጫ (ለአማካሪ እና ኮንትራክተር)

ለተጨማሪ መረጃ

eacecivil@gmail.com or 0115521248 or 0901250000 መጠየቅ ይችላሉ።