የሃዘን መግለጫ

የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር የቀድሞው ኘሬዚዱንት ኢንጂነር ፈቃደ ኃይሌ (Fellow Engineer Fekade Haile) ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ልባዊ ሃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን!!

ኢንጂነር ፈቃደ ኃይሌ ማህበሩን በፕሬዝዳንትነት (ከ2005 እስከ 2011 እ.ኤ.አ ) እና በተለያዩ ንዑስ ኮሚቴዎች አገልግለዋል በተለይም የሞያውን ስነ-መግባር እንዲስፋፋ እና እንዲተገበር ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር።

የኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ የውልደት የትምህርትና የሥራ ሁኔታ አጭር ታሪክ

ፍቃዱ ሃይሌ ሐምሌ 1 ቀን 1953 ዓ.ም ከእናቱ ከወ/ሮ በየነች መኮንንና ከአባቱ ከአቶ ቦጋለ ሶዶ በአዲስ አበባ ከተማ ፍለውሃ ኦርማ ገራዥ አካባቢ ተወለደ ፡፡

ፍቃዱ ክእናቱ ከተወለዱት አምስት ልጆች ውስጥ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን በአባቱ በኩል ታላቅ ወንድም አለው ፡፡ በእናቱ ከተወለዱት ውስጥ ለአቅመ አዳምና ሄዋን የደረሱት ሶስት ብቻ ናቸው፡፡ ቤተሰቦቹ በአነስተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የነበሩ በመሆኑ መሰረታዊውን ትምህርት ለማግኘት በጣም ይቸገር ነበር ፡፡ ለትምህርት ያለው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ የአባቱን ታናሽ ወንድም አቶ ሓይሌ ሶዶን በራሱ ተነሳሽነት በመጠየቅ እሳቸውም የተማሩ በመሆናቸው ለትምህርት ያለውን ፍላጎት በመመልከት የግል ትምህርት ቤት ከፍለው ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል በሁዋላም በጉዋደኛቸው አማካይነት ፍቃዱ ሃይሌ ተብሎ የመንግሥት ት/ቤት ተማሪ በማድረግ እሰከ ዩንቨርሲቲ ድረስ ትምህርቱን እነድዲያጠናቅቅ አድርገው ለወግ ለማዕረግ አብቅተውታል ፡፡

ወጣቱ ፍቃዱ ለትምህርት ካለው ከፍተኛ ፍቅር የተነሳ ትምህርቱን ሌት ከቀን በማጥናት በከፍተኛ ውጤት በአብዛኛው ከክፍሉና ከትመህርት ቤቱ አንደኛ በመውጣትና በሶስቱም ብሄራዊ ፈተናዎች በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ በማለፍ

  1. የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል በ2 ዓመት( 1958 ና 1959 ዓ.ም.)  በተስፋ ትምህርት ቤት ቦሌ ወሎ ሰፈር ፣ ከ5ኛ እሰከ 8ኛ ክፍል በፊታውራሪ ላቀ አድገህ ትምህርት ቤት (1960 እስከ 1964 ዓ.ም.)
  2. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት  በሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 9ኛ ና 10ኛ ክፍል በዳግማዊ ምንሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 11ኛና  12ኛ ክፍል  ከ 1965 ዓ.ም. እስከ 1971 ዓ.ም. ( የእድገት በህብረትና የዕውቀትና የሥራ ዘመቻ ተሳታፊ በመሆን ከ1967 ዓ.ም. 1968 ዓ.ም.  መጨረሻ የዘመቻ ግዳጁን በመማጠናቀቅ ሰርተፊኬት ተሰጥቶታል)
  3. በቢኤስ ሲ ዲገሪ በሲቪል ምህንድስና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ 1975 ዓ.ም. ተመርቁዋል

ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ በ1978 ዓም አብሮ አደጉ ከሆነችው ከመምህርት ወ/ሮ በቀለች ተፈራ ጋር ህጋዊ ጋብቻውን በመፈጸም 4 ወንዶችና 3 ሴት ልጆች በማፍራት ትልቅ ቤተሰብ በመመሥረት ከባለቤቱ ጋር በተደረገ የተሳካ ሃላፊነት በመወጣት ሁሉንም ልጆቻቸውን በዲግሪ በማስመረቅ ቤተሰቡን የምሁራን ቤት የሚል ቅጽያ በጎረቤቶቻቸውና በወዳጅ ዘመዶቻቸው አግኝተዋል፡፡

ከኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ የተወለዱት ልጆችም በቅደም ተከተል

1ኛ አንተነህ ፍቃዱ ሃይሌ (ኢኮኖሚስት)

2ኛ ፍጹም ፍቃዱ ሃይሌ   (ሲቪል መሃንዲስ)

3ኛ ቤዛዊት ፍቃዱ ሃይሌ  (ሲቪለ መሃንዲስ)

4ኛ ፍሬህይወት ፍቃዱ ሃይሌ (የህክምናዶክተር)

5ኛ ቢኒያም ፍቃዱ ሃይሌ (ሲቪል ምህንድስና በመማር ላይ)

6ኛ ሰላማዊት ቃዱ ሃይሌ (ሕክምና በመማር ላይ)

7ኛ ምንያህል ፍቃዱ ሃይሌ ( ኮምፒውተር ኢነጂነሪንግ በመማር ላይ ) ናቸው፡፡

ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ  የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን በሲቪል ምህንድስና ሙያ ካጠናቀቀ በሁዋላ በሙያው ከ38 ዓመታት በላይ አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ልምድ አካብቱዋል፡፡ በነዚህ ዓመታት ውስጥም በአብዛኛው የሠራው በመንገድ ግንባታና ኮንትራት አስተዳደር ፕሮጄክቶች ላይ ነው፡፡ በነዚህም ዓመታት በመንገድ ግንባታ፣ በግድብ ግንባታ፤በአውሮፕላን ማረፊያዎች ግንባታ፣ በተለያዩ ድልድዮች ግንባታ፣ በፕሮጄክት መኖሪያ ቤቶች ካምፕ ግንባታ፣ በኮንትራት አስተዳደርና ማናጅሜንት ፣ እረፍት በመውሰድ በአማካሪነት የዲዛይን ማንዋሎችን በማዘጋጀት ከሌሎች ሙያተኞች ጋር በመሥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቱዋል፡፡

 ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ ከተራ መሃንዲስነት በመጀመር ደረጃ በደረጃ በፕሮጄክቶች ተጠሪ መሃንዲስነት፣ በፕሮጄክቶች ሥራ አሥኪያጅነት ፤ በመንገድ ጥገና አገር አቀፍ ዲስትሪክት ሥራ አሥኪያጅነት ፣በኢመባ ዋናው መሃንዲስ ቢሮ በከፍተኛ የቢሮ መሃንዲስነት፣ በኢመባ ዋና መሃንዲስነትና ምክትል ሥራ አሥኪያጅነት ፣ በኢመባ ዋና ሥራ አሥኪያጅ የቴክኒክ ዋና አማካሪነት፣ የመጀመሪያው የኢመባ የመንገድ ልማት ፕሮግራም  አስተባባሪነት፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅ በመሆን ባለማቐረጥ በተከታታይ ከ አራት የከተማችን ከንቲቦች ጋር ( ከአቶ አርከበ ዑቅባይ፤ ከአቶ ብርሃነ ደሬሳ፤  ከአቶ ኩማ ደምቅሳና ከአቶ ድሪባ ኩማ ) ና በምክትል ቢሮ ሃላፊነት ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የአቶ ድሪባ ኩማ የቴክኒክ አማካሪ በመሆን ከማገልገሉም በላይ በነዚህ ጊዚያት ውስጥ ከነዚህ ሃላፊነቶች በተጨማሪ ከ 10 በላይ የሆኑ መሥሪያ ቤቶች የቦርድ ሰብሳቢና አባል በመሆን ከፍተኛ አገልግሎት አበርክቱዋል፡፡

ኢነጂነር ፍቃዱ ሃይሌ ለሙያው ካለው ከፍተኛ ፍቅርና ክብር የተነሳ በሌለው ጊዜ የኢትዮጵያ ሲቪል መሃንዲሶች አባል ፣ አመራርና በመጨረሻ ፕሬዚደንት በመሆን ለ 6 ዓመታት በማገልገል በማህበሩ የሚሰጠው  ከፍተኛ የሲቪል ምሀhንድስና የአገልግሎት መጠሪያ የፌሎ ኢንጂነር ስም ተሰጥቶታል፡ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ ከ መጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከመንግሥት ስራና ሃላፊነት በጡረታ ተገልሎ በግል አማካሪነት በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ሀ) የኢንጂነር ፍቃዱን ትምህርትና ሥልጠናን በተመለከተ

ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ ከላይ በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ በበርካታ ሃገሮች ውስጥ ከሙያው ጋር ግንኙነት ያላቸው ጉብኝቶችና ሥልጠናዎች ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ ዲፕሎሞችና ሰርተፊኬቶች ተቀብሉዋል ፡ በሚቀጥለው ዝርዝር ከቅርብ ዓመታት ወደ ራቁት ዓመታት ተራ ጥቂቶቹ ተመላክተዋል፡፡

  1.  ከኢትዮጵያ ሲቪል መሃንዲሶች ማኅበር ፤ ለሃገራቸው ኢትዮጵያ ላበረከቱተት ከፍተኛ የሆነ የምህንድስና አገልግሎትና ለኢትዮጵያ ሲቪል ምህንድስና ማህበር ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተመረጡት 12 የሲቪል ምህንድስና ባለሙያዎች አንዱ በመሆን የህይወት ዘመን የላቀ የምህንድስና አገልግሎት የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት በሰኔ ወር 2013 ዓም ተበርክቶለጻል ፡፡
  2. በዓለም ዐቀፍ የሠራተኛ ድረጅት (ILO) በኢንተርናሽናለ ሥልጠና ማዕከል (ICT) ; አዲስ አበባ በተሰጠ “ International Labour Standards and Constitutional obligations”   ሥልጠና በመሳተፍ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ሕዳር 2008 ዓ.ም.
  3. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቅም ግንባታ ቢሮና በከተማ ሥራ አመራር ኢኒስቲቲዩት ፤ በመንግሥት ፖሊሲዎችና እስትራተጂዎች ዙሪያ የተሰጠ የአመራር ሥልጠና ሰርተፊኬት ሚያዚያ 2001 ዓ.ም.
  4.  ከፍተኛ ዲፕሎማ በከተማ ትራንስፖርት ላይ በመስከረም 2000 ዓ.ም. ከሉንድ ዩንቨርስቲ ስዊድን
  5. ሰርተፊኬት በኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ከደቡብ ኮሪያ በህዳር 1999 ዓ.ም.
  6. ሰርተፊኬት በኮንስትራክሽን ክሌይም ግልግልና ዳኝነት ላይ በእንግሊዝ መንግሥት የልማት ተራድዖ መሥሪያ ቤት የተዘጋጀ በአዲስ አበባ በየካቲት 1998 ዓ.ም.
  7. ሰርተፊኬት በከተማ ትራንስፖርት ሪፎርምና ደንብ ላይ በዓለም ባንክ የተዘጋጀ ዳሬሰላም ታንዛኒያ በሃምሌ 1997 ዓ.ም.
  8. ማዘጋጃቤታዊ የልምድ ለውውጥ ጉብኝቶችና ሥልጠናዎች በፈንሳይ ሊዮን ፣ በቻይና ቤጂንግ ሻንጋይና ሁናን ፣ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ፕሪቶሪያ  ደርባን እና ኬፕታውን  1997 ዓ.ም.
  9. ከኢትዮጵያ ሲቪል መሃንዲሶች ማኅበር ፤ ለኢትዮጵያ ሲቪል ምህንድስና ሥራና ለማህበሩ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የፌሎ ማዕረግ ዲፐሎማ መስከረም 8 ቀን 1997 ዓ.ም.
  10.  ኮንትራት አስተዳደርና የመንገድ ዲዛይን በተመለከተ ጉብኝቶችና ሥልጠናዎች በአሜሪካ ዋሽንግተንና ኒውዎርክ በፈረንሳይ ፓሪስ፣ በጀርመንና ኔዘርላንድ  19 87 ዓ.ም.
  11.  ሰርተፊኬት በኮንትራት ግዢ ሥርዓት ላይ የፊዲክ ቀይ መጽሃፍንና የዓለም ባንክ የጨረታ እስታንዳርድን መሰረት ባደረገ ስልጠና በአዲስ አበባ በህዳር በ1991ዓ.ም. 
  12.  በኮንትራት አስተዳደር ሥልጠና በአሜሪካ ኒው ጀርሲ በሊውስ በርገር አለማቀፍ ኩባንያ በ1987 ዓ.ም.
  13.  ሰርተፊኬት በድልድይ ዲዛይን ኢንጂነሪንግ ፣ በመንገድ ዲዛይንና በጂኦቴክኒካል ኢንጂነሪንግ በጃፓን መንግሥት( ጃይካ) ና በትራንስ‹ፖርት ዲዛይን ኢንተርፕራይዝ (ቲሲዲኢ) የተዘጋጀ በየካቲት 1987 ዓ.ም.)
  14.  ሰርተፊኬት በመንገድ ጥገናና አስተዳደር ና በኮንትራት  አስተዳደር በክራውን ኤጀንት አዘጋጅነት በእንግሊዝ  ሎንዶን  በ  1986 ዓ.ም.
  15.  ሰርተፊኬት በእሰፋልት ልባስ መንገዶች ላይ ከኖቲንግሃም ዩኒቨርስቲ እንግሊዝ ሃገር በ1986 ዓ.ም.
  16.  ሰርተፊኬት በድንጋይ ፍንዳታ ቴክኖሎጂ በፊንላንድ የመንገድ አስተዳደር ባለሙያዎች አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በ1984 ዓ.ም.
  17.  ሰርተፊኬት በኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ( በሲቪል ሥራዎች ) ጃፓን ኦሳካ (ጃይካ) ህዳር 1982 ዓ.ም.
  18.  ሰርተፊኬት በኮንስትራክሽን ፕሮጄክት ማናጅሜንት  በኢትዮጵ ማናጅሜንት ኢንስቲቲዩት ደብረዘይት በ1981 ዓ.ም.

ለ) ኢንጂነር ፍቃዱ ያከናወናቸው ዋና ዋና ሙያዊ ተሳትፎና ሥራዎችን  በተመለከተ

ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ በሙያው ያከናወናቸው ዋና ዋና ሥራዎች

1. በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ በዋና አገናኝ መንገዶችና የከተማ መንገዶች በዲዛይን፣በግንባታና በኮንትራት አስተዳደር  ዋና ዋና ፕሮጄክቶች ላይ በቴክኒክና በአመራር ሰጭነት

2. በአዲስ አበባ ከተማና በፌደራል በሚገኙ የተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በተቐቐሙ የቴክኒክ ኮሚቴዎችና ቦርዶች አመራር ላይ ተሳታፊ በመሆን ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት

  • የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የቦርድ አባል ከግንቦተ 1 ቀን 2008 ዓ.ም እሰከ ሐምሌ 2009 ዓ.ም
  • የሸገር አውቶቡስ ድርጅት የቦርድ አባል ነሃሴ 2007 ዓ.ም.ጀምሮ ሐምሌ 2008 ዓ.ም
  • የትራንስፖርት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የቦርድ አባል ነሃሴ 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 2008 ዓ.ም.
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማሶገድ ኤጄንሲ የቦርድ አባል ከግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2008 ዓ.ም.
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእግርኳስ ክለብ የቦርድ አባል 2006 ዓ.ም እሰከ ሐምሌ 2008 ዓ.ም
  • የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጄክት ጽ/ቤት ቦርድ አባል ከነሓሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም እስከ ሓምሌ 2008 ዓ.ም
  • የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ አባል ከሐምሌ 6 ቀን 2003 ዓ.ም. እስከ ሐምሌ 2008 ዓ.ም.
  • የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የኢትዮጵ ሲቪል መሃንዲሶች ማህበርን በመወከል ከግንቦት 8 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም 2007 ዓ.ም.
  • የጥቁር አባይ ኮንስትራክሽን አክስዮን ማህበር የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ከጥር 5 ቀን 2003 ዓ.ም. የካቲት 2006 ዓ.ም
  • የኢትዮጵ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ አባል ከመስከረም 27 ቀን 2002 ዓ.ም እስከ የካቲት 2009 ዓ.ም.
  • በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር  የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሊዝ ቦርድ አባል ከጥቅምት 1 ቀን 2001 ዓ.ም እሰከ 2005 ዓ.ም
  • የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የሥራ አመራር ቦርድ አባል ከታህሣሥ 1998 ዓ.ም. – ሀምሌ 2008 ዓ.ም
  • የባቱ ኮንስትራክሽን አክስዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ከጥቅምት 29 ቀን 1997 ዓ.ም እስከ ጥር 2003 ዓ.ም.

3. በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣንን የ 15 ዓመት የመንገድ ልማት ፕሮግራም በ1996 ዓ.ም. በመቅረጽ የከተማዋን ዋና ዋና መንገዶች፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችንና ዘመናዊ የከተማ መንገዶች ዲዛይን፣ ቁጥጥርና ኮንትራት አስተዳደር ፕሮጄክቶች በመምራት ያለውን እውቀትና ልምድ በ ማበርከት ከተማውን የመንገድ አውታር በ1995 ዓ.ም ሲረከብ ከነበረበት 1500 ኪሎ ሜትር 6000  ኪሎ ሜትር በ14 ዓመታት ሃላፊነቱ እንዲደርስ ያደረገ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ  የሚከተሉትን ብርቅዬ የከተማችን መንገዶች በመገንባትና በማስገንባት አሻራውን አኑርዋል

የመንገድ ስም

አጠቃላይ ስፋት ሜትር

አጠቃላይ እርዝመት ሜትር

1995 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

1

አደይ አበባ ቀለበት መንገድ አዲሱ ሰፈር

10

850

2

ኮልፌ አደባባይ ኮልፌ ፊሊጶስ መንገድ

10

1,000

3

መካኒሳ ድልድይ መካኒሳ ቀለበት መንገድ

20

1,100

4

አስፋው ተክሌ እህል በረንዳ መንገድ

10

1,350

5

ጎፋ ገብርኤል ጎፋ መብራት ሃይል

20

1,700

       6,000

1996 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

6

የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ ከቃሊቲ አደባባይ ቦሌ ዲያስፖራ አደባባይ መንገድ

40

6,354

7

ከመሪ አያት መንገድ

15

1,200

8

ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ

10

1,500

9

የወሎ ሰፈር ጎተራ መንገድ

30

2,100

     11,154

1997 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

10

ደብረዘይት መንገድ ቀለበት መነገድ ቡልቡላ ድልድይ

20

500

11

የአድዋ ድልድይ  አደዋ አደባባይ ( መገናኛ)

25

2,400

12

መስቀል ፍላወር ሆቴል ደብረዘይት መንገድ

25

500

13

ከዑራኤል አትላስ ቦሌ ብራስ ቀለበት መንገድ

30

3,200

14

አቦ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ መድሃኒዓለም ቤ/ክ

25

2,000

8,600

1998 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

15

ከጎፋ ማዞሪያ ቂርቆስ

40

2,100

16

ከአለርት ሆስፒታል ቀለበት መንገድ ቀራንዮ

20

2,300

17

ከየረር በር በጉረድ ሾላ ሳህሊተ ምህረት

25

2,300

18

መካኒሳ ቀለበት መንገድ አደባባይ ጃሞ መስታወት ፋብሪካ

40

2,200

8,900

1999 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

19

ቦሌ መድሃኒዓለምአደባባይ  ቦሌ መንገድ (ዓለም ህንጻ)

16.50

800

20

ቦሌ መድሃኒዓለምአደባባይ ሓያት ሆስፒታለ

16.50

1,000

1,800

2000 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

21

ከሳህሊተ ምህረት አደባባይ ሰሜን ተርሚናል መንገድ

20

740

22

ላፍቶ ለቡ ቀለበት መንገድ መስታወት ፋብሪካ

30

4,100

23

ከአቦ ቀለበት መንገድ አደባባይ ደብረዘይት መንገድ

15

300

5,140

2001 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

24

የጎተራ ትራፊክ ማሳለጫ

40

8,100

25

ከሲኤም ሲ አደባባይ ሰሚት ሬዲዮ ቤከን

24

4500

26

ከቦሌ ሚካኤል አደባባይ ቡልቡላ መድሃኒዓለም

10

6000

27

የጦር ሃይሎች አደባባይና የታክሲ ተርሚናለ ግንባታ

50

800

28

ከአክሱም ሆቴል ቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

25

1,700

21,100

ተራ ቁጥር

የመንገድ ስም

አጠቃላይ ስፋት ሜትር

አጠቃላይ እርዝመት ሜትር

2002 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

29

ከአፍሪካ ህብረት በፑሽኪን መካኒሳ ቀለበት መንገድ  አደባባይ

30

4,420

30

ከ3 ቁጥር ማዞሪያ በብስራተ ገብርኤል ደሴ ሆቴል/ ከካርል አደባባይ ፑሽኪን አደባባይ

30

4,100

31

የካቲት 12 አደባባይ አፍንጮ በር ሰሜን ሆቴል

30

1600

32

ከጎፋ ገብርኤል በጎፋ ካምፕ መካኒሳ ቀለበት መንገድ አደባባይ

30

2200

33

ከመገናኛ ቀበና አራት ኪሎ/ ቀበና ምንሊከ ሆስፒታል

40

5800

34

ከኮካኮላ ማዞሪያ በአብነት ተክለሃይማኖት

30

2500

35

ከኔዘርላንድ አደባባይ የሺ ደበሌ አምቦ መንገድ

40

5900

    29,920

2003 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

36

ከገርጂ ቀለበት መንገድ አደባባይ ወረዳ 17 ጤና ጣቢያ

30

1200

37

ከየረር በር አንበሳ ጋራዥ ለም ሆቴሌ ሾላ ገበያ

30

3499

38

ከመገናኛ በሲኤም ሲ አያት የቀኝ መንገድ

20

8,200

39

መካኒሳ ጃሞ መስታወት ፋብሪካ ሰበታ መንገድ

30

4,400

40

ከኢምፔሪያል ሆቴል የረር በር

30

3100

41

የሳሪስ ድልድይ ኮካኮላ መገንጠያ መንገድ

40

1,000

42

ከዐድዋ ድልድይ በላይፕዚነግ አደባባይ አሪ በከንቱ/ከገደራ አደባባይ ካዛንቺስ

       20

       3,450

    27,299

2004 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

43

ከዊንጌት ትራፊክ ሰፈር አስኮ አዲሱ ሰፈር

44

ከዓለም ባንክ ሰፈር የሺ ደበሌ

30

3460

45

ከየረር በር የረር ጎሮ ፍሳሽ ማጣሪያ

30

5200

46

ከመስቀል አደባባይ ቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ

40

9000

47

ከዊንጌት ቀለበት መንገድ አደባባይ ጎጃም በር

40

       4,082

21,742

2005 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

48

የአያት ጣፎ ካራ መንገድ

30

7000

49

ከውሃ ሃብት አድዋ ድልድይ እንግሊዝ ኤምባሲ

30

2034

50

ከአስኮ አዲሱ ሰፈር ጊዮርጊስ/ ፊለጶስ ኮልፌ

20

2200

51

አያትና አቃቂ አካባቢ የማስፋፊያ የጠጠር መንገድ

10

25000

52

አቃቂ ለቡ ፉሪናየሺደበሌ አካባቢ የማስፋፊያ የጠጠር መንገደ

10

25000

53

ከሰሜን የአውቶቡስ መናኸሪያ ኮቶቤ ካራ

40

5,600

47,434

2006 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

54

5 ቁጥር ማዞሪያ ገ/ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

20

800

55

ቦሌ ሰሚት ኮንደሚኒየም የውስጥ መንገድ

20/25

5000

56

ጅማ መንገድ ፊሊጶስ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት

20

2000

57

ከአያት  ጎሮ አደባባይ

24

6100

58

ከጦር ሃይሎች ቀለበት መንገድ አደባባይ ቀራኒዮ

30

2,800

59

ከዲያስፖራ አደባባይ ሰሜን ተርሚናል

30

2100

60

ከዳማ ሆቴል ሃና ማሪያም የቀለበት መንገድ ድልድይ

30

3000

61

መገናኛ አያት የግራው መንገድ

20

8200

62

ዊንጌት አስኮ ሚኪሊላንድ

30

2250

63

ከመስቀል አደባባይ ቦሌ ቀለበት መንገድ አደባባይ

40

5500

37,750

ተራ ቁ

2007 ዓ.ም የተጠናቀቁ መንገዶች

ስፋት ሜትር

እርዝመት ሜትር

64

ሲቲ ቲፕ(ሚካኤል) ቀለበት መንገድ አደባባይ ብሥራተ ገብርኤል አደባባይ

30

2690

65

አቡዋሬ አደባባይ ጀርመን ድልድይ ባልደራስ መንገድ

20

1000

66

ከአየር ጤና ኪዳነ ምህረት አለም ባንክ የሺ ደበሌ መንገድ

40

5180

67

ስድስት ኪሎ ፈረንሳይ ኤምባሲ ጉራራ

30/25

4134

68

ከእንጦጦ ኬላ እንጦጦ ራጉኤል መንገድ

10

3200

69

አቃቂ ቃሊተ ደብረዘይት መንገድ ፍሬይት ተርሚናል

20/40

2065

70

ከቦሌ ሚካኤል ቦሌ ሩዋንዳ/ መስቀል ፍላወር ቦሌ ሚካኤል

20/30

2950

71

ከቃሊቲ ዋና መንገድ አቃቂ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

40

2300

72

ከአበበ ቢቂላ እስታዲዮም ታይዋን ድልድይ ኮልፌ ቀለበት መ

25

1600

73

ከአበራ ሆቴል ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን መንገድ

20

980

74

ከዲያስፖራ አደባባይ ሰሜን ተርሚናል

30

2000

28,099

2008 ዓ.ም የተጠናቀቁና በግንባታ ላይ የነበሩ

75

ከልደታ በአብነት መርካቶ አቡነ ጴጥሮስ ጊየርጊስ

30/40

4000

76

ከማዕድን ሚኒስቴር በመገናኛ ሜክሲኮ ኮካ መገንጠያ

40

8800

77

ከጎሮ አደባባይ አይ ሲቲ ፓርክ

24

3200

78

አቃቂ ለቡ አይ ሲቲ ፓርክ 2ኛ ቀለበት መንገድ

60

28100

79

አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ዊንጌት አደባባይ

30

5600

80

ከጣፎ አደባባይ ለገዳዲ የቖሻሻ ማሶገጃ ሥፍራ

16.50/10

8000

81

ከፈረንሳይ ጉራራ ኮቶቤ ኪዳነ ምህረት

15

3500

82

ልደታ ጸበል ቡልጋሪያ እስራኤል ጋራዥ

30

5200

83

ፊሊጶስ ድልድይና መቃረቢያ መንገድ

20

1500

84

ከሲኤምሲ አደባባይ በካራመንገድ ከቶቤ ማረያም

40

200

85

ከደብረዘይት መንገድ ፍሬይት ተርሚናል

20

2160

86

የረር ጎሮ ሲኤምሲ ወንድራድ ት/ቤት

20

5756

87

ተ/ሃይማኖት አደባባይ ቤተ መንግሥት

30

2065

88

ጉርድ ሾላ ሰሚት የካ ቦሌ

30

8300

89

ከወሰን መንገድ ኮቶቤ ወንድራድ ት/ቤት

20

800

90

ከአያት አደባባይ ሰን ሻይን ኮንዶ አያት ጎሮ መንገድ

20/30

4420

91

ካራሎ ኮቶቤ መንገድ

50

300

92

ብሥራተ ገብርኤል አደባባይ መካኒሳ አቦ አደባባይ

30

1500

93

ከጃንሜዳ በቅድስተ ማሪያም ፒያሳ መንገድ

25

1300

94

ሬዲዮ ቤከን ( ሰሚት ኮንዶሚነየም) ፍሳሽ ማጣሪያ

50

1500

95

ሽሮ ሜዳ ኪዳነ ምህረት

20

2100

96

ቂሊንጦ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ኮየ ፍቼ አደባባይ

40

1200

97

የሲኤምሲ ሚካኤል መሸጋገሪያ ድልድይና መቃረቢያ መንገድ

35

600

98

የጉርድ ሾላ አያት መሸጋገሪያ ድልድይና መቃረቢያ መንገድ

45

700

99

ትራንስፖርት ባለሥልጣን ውሃና ፍሳሽ ወረዳ 17 ጤና ጣቢያ

30

3500

100

አቃቂ ዋና ድልድይና መቃረቢያ መንገድ

50

200

101

ከቃሊቲ መንገድ ትራንስፖርት አደባባይ አቃቂ ቱሉ ዲምቱ መገንጠያ አደባባይ ዲዛይን በማጠናቀቅና ፋይናንስ በማግኘትና የግንባታ ኮንትራት መፈረም

50

11000

102

ከቃሊቲ መንገድ ትራንስፖርት አደባባይ ኮዬ ፈቼ አደባባይ  ዲዛይን በማጠናቀቅ ፋይናንስ በማግኘትና የግንባታ ኮንትራት መፈረም

40

11000

103

ከፑሽኪን አደባባይ በቄራ ጎተራ መንገድ ዲዛይን ማጠናቀቅና ፋይናንስ የማግኘት ድርድር ላይ

40

3500

130,801

ጠቅላላ

385,739

4. በአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ፕሮጄክቶች ውስጥ የመሰረተ ልማት ቅንጅትን በመምራት ቤቶቹ የመንገድ መሰረተ ልማት፣ የቴሌፎን፣የውሃ፣ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት እንዲሙዋላላቸው በማድረግ

ተራ ቁ

 የጋራ መኖሪያ መንደር ስም

የመንገድ

ስፋት

ሜትር

የመንገድ እርዝመት ሜትር

የኮብል መንገዶች

1

በልደታ መልሶ ግንበታ የጋራ መኖሪያ

10/16/21

    5000

2

ጃሞ ቁጥር 2 የኮብል መንገድ

10/16/21

    3695

3

ጃሞ ቁጥር 3 የኮብል መንገድ

10/16/21

    3739

4

ቦሌ አያት 2 የኮብል መንገድ

10/16/21

   17608

5

ቦሌ ሰሚት  የኮብል መንገድ

10

   19442

6

የካ አያት 2 ኮብል መንገድ

10/15/21

   13383

7

በየካ አባዶ 1፤2 እና 3 ኮብል መንገድ

16/21/25

   23000

8

መካኒሳ ቆጣሪ ኮብል መንገድ

15/21/25/30

    3550

9

ካራ ቆሬ ኮብል መንገድ

10/16/25

    1463

10

ገላን 3 ኮብል መንገድ

10/16/21

   11914

11

ቦሌ አያት 5 ኮብል መንገድ

10

     700

12

ቦሌ ሰሚት 2  የኮብል መንገድ

10 

    2249

13

ባሻ ወልዴ ችሎት የኮብል መንገድ

10

    2466

14

ላፍቶ 2ሀ/2ለ ኮብል መንገድ

10

    2353

15

የካ አያት 3 ኮብል መንገድ

10

     815

16

በቦሌ ቡልቡላ ኮብል መንገድ

10/16/21

    6053

17

በቦሌ አራብሳ 1 እና 2 ኮብል መንገድ

10/12/16/25

   18240

18

ገነት መናፈሻ ኮንዶ ኮብል መንገድ

10/16/22

    1823

19

ደግነት ኮብል መንገድ

10

     718

20

ቱሉ ዲምቱ  ኮብል መንገድ

10/16/21

   18822

21

ቅሊንጦ  ኮብል መንገድ

10/20/25

    6780

22

ለቡ ኮብል መንገድ

10

     483

23

ገላን 1 እና 2 ኮብል መንገድ

10

    1500

 165,796

አስፋልት መንገዶች

1

በልደታ መልሶ ግንበታ የጋራ መኖሪያ

20

    3500

2

ጃሞ ቁጥር 2 የአስፋልት መንገድ

20/30

    2500

3

ጃሞ ቁጥር 3 የአስፋልት መንገድ

20/30

    1262

4

ቦሌ ሰሚት  የአስፋልት መንገድ

20/30

    5129

5

የካ አባዶ 1፤2 እና 3 አስፋልት መንገድ

21/30

    3730

6

ቦሌ ቡልቡላ አስፋልት መንገድ

25/30/50

    4012

7

ቦሌ አራብሳ 1 እና 2 አስፋልት መንገድ

30/40

    7642

8

ገላን 3 አስፋልት መንገድ

10/21/30

    3587

9

ሰንጋተራ 40/60 አስፋልት መንገድ

10/20/25

     653

ተራ ቁ

 የጋራ መኖሪያ መንደር ስም

የመንገድ

ስፋት

ሜትር

የመንገድ እርዝመት ሜትር

10

ክራውን 40/60 አስፋልት መንገድ

10/20/25

    1602

11

ገነት መናፈሻ አስፋልት መንገድ

10/16/22

    1823

12

ካራ ቆሬ አስፋልት መንገድ

16/21

    1555

13

ቅሊንጦ  አስፋልት መንገድ

16/25

    2600

14

ኮዬ ፈጨ  አስፋልት መንገድ

30/40

    4700

15

እህል ንግድ 40/60 አስፋልት መንገድ

10/20

    2171

  46,466

5. የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ጥንስስ ጽ/ቤትን በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ውስጥ በቅድሚያ በማቐቐም በመቀጠልም የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሲቐቐም ጽ/ቤቱን እንዲዛወር ማድረግና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ አባልና የቦርዱ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆንና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጄክትን የመንገድና የባቡር መሰረተ ልማት በቅንጅት በመምራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርና የኢትዮጂቡቲን ዋና ባቡር በማስጀመር ታሪካዊ አሻራውን አስቀምጡዋል

6. የአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ አቅጣጫ ስያሜ አመልካች ዘመናዊ ምሰሶዎችን በሌላው ዓለም ያለውን ተሞክሮ በመውሰድ ከቀለበት መንገዱ በመጀመር ሁሉም የከተማዋ መንገዶች እንዲኖራቸው በማድረግ ለከተማችን መሰረት ጥሉዋል

7. የአዲስ አበባ ከተማ መስቀለኛ መንገዶች የትራፊክ መብራት እንዲኖራቸው፤ የከተማዋ መንገዶች ከዘመናዊ የመንገድ መብራት ጋር እነድዲገነቡና  የእግረኛ ማቐረጫና የሌን መክፈያ የቀለም ቅብ ሥራ በከተማችን በማስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጉዋል ፡ የእግረኛ የመከለያ አጥሮች በስፋት የተገነቡትም በኢንጂነር የአመራር ወቅት ነው  

8. በኢመባና በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ለጥናት የሚዘጋጁ የዲዛይን የአዋጭነት ጥናት ና የሌሎች ጥናቶችን የሥራ መዘርዝር ጽፎ በማዘጋጀት

9. በኢመባና በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በኮንትራት አስተዳደርና በኮንትራክተሮች የተነሱ የይገባኛል (የክሌይም) ጥያቄዎችን  በክሌይም ትንተና ኮሚቴ በመሳተፍ ምላሽ በመስጠት

10. የኢመባን 1995 ዓ.ም እና የአዲስ አበባ ከተማመንገዶች ባለሥልጣንን የ 1996 ዓ.ም. የዲዛይን ማኑዋሎች በሙያተኝነት ከአማካሪዎች ጋር በማዘጋጀት

11. የኢመባን የመንገድ ጥገና እስታንዳርድ በ1991 ዓ.ም. ና የድልድይ ኢንስፔክሽን መመሪያ በ1993 ዓ.ም. በኢመባ የተቐቐመውን የቴክኒክ ኮሚቴ በመምራት ማዘጋጀት

መ)  የሠራቸውን ሥራዎችና የሠራባቸውን ቦታዎች በተመለከተ

 1) ከነሃሴ 2008 - የካቲት 2012 ዓ.ም.

    በምክትል ቢሮ ሃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የቴክኒክ አማካሪ

 2) ከየካቲት 1995 - ሐምሌ 2008 ዓ.ም (ለ14 ዓመታት)

    የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅ

 3) ከነሃሴ 1989 - የካቲት 1995 ዓ.ም.

የኢትዮጰ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሲኒየር አማካሪና የአንደኛው የመንገድ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ

 4) ከግንቦት 1987 – ሀምሌ 1989 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና መሃንዲስና ምክትል ሥራ አስኪያጅ በዚህ ጊዜ ውስጥ በዋነኛነት

4.1 የመቀሌን፤ የጎንደርንና የላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሥራዎች አስጀምሩዋል

 4.2  ከአዲስ አበባ ወደ 5 ቱም የመውጫ አቅጣጫ የሚገኙ የዋና ዋና መንገዶችን ዲዛይን በውጭ አገር አማካሪ መሃንዲሶች እንዲዘጋጅ አድርጉዋል

 4.3 የኢመባ የ1995 ዓ.ም. የዲዛይን ማንዋሎችና እስፔስፊኬሽን እንዲዘጋጅ የውጭ አማካሪ አጥኝዎች በጨረታ አወዳድሮ በመቅጠር ሥራውን አስጀምሮ በጥናቱም ሙሉ ጊዜውን በመስጠት ተሳትፎአል 

 5) ​ከነሃሴ 1986 - ሚያዚያ 1987 ዓ.ም.

በኢመባ በዋናው መሃንዲስ ቢሮ ዋና የቢሮ መሃንዲስ

 6) ​ከታህሳስ 1984 - ሀምሌ 1986 ዓ.ም.

በትግራይ ክልል የኢትዮጵ መንገዶች ባለሥልጣን የመንገድ ሃላፊ በመሆን የአዲግራት ዲስትሪክት ዋና ሥራ አሥኪያጅ

 7) ​ከግንቦት 1983 - ታህሳስ 1984 ዓ.ም.

የኢመባ የኦፕሬሽን መምሪያ የቢሮ መሃንዲስ

 8) ​ከታህሳስ 1982 - ግንቦት 1983 ዓ.ም.

በኢመባ የዳህላክ የአውሮፕላን ማረፊያ (3000 ሜትር በ 45ሜትር) ግንባታ ዋና ሥራ አሥኪያጅ

 9) ​ከሰኔ 1981 - ህዳር 1982 ዓ.ም.

በኢመባ የሚሌ አሰብ ዋና መንገድ የመልሶ ግንባታ ፕሮጄክት (110 ኪ.ሜ በ 7 ሜትር ስፋት) ዋና ሥራ አሥኪያጅ

 10) ​ከመጋቢት 1982 - ሰኔ 1982 ዓ.ም.

በኢመባ የሚሌ አሰብ መንገድ ፕሮጄክት ሥራ አሥኪያጅ ሆነው በተደራቢነት የ አሰብ የተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ማረፊያ የኮንክሪት አስፋልት ግንባታ ፕሮጄክት ( 300 ሜትር በ 90 ሜትር ) ሥራ አሥኪያጅ

 11) ​ከግንቦት 1980 - ጥር 1981 ዓ.ም.

በኢመባ የቦርከና ግድብ ቁጥር 2 ዋና ሥራ አሥኪያጅ

 12) ከየካቲት 1979 – 1980 ዓ.ም.

በኢመባ የጎሬ ቴፒ የጠጠር መንገድ ግንባታ ፕሮጄክት (143 ኪ.ሜ በ 7 ሜትር) ፕሮጄክት መሃንዲስ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፈንድ ጀርመን ተቆጣጣሪ መሃንዲስ

 13) መስከረም  1978 – ጥር  1979 ዓ.ም.

በኢመባ የጎሬ ጋምቤላ የጠጠር መንገድ (42.5 ኪ ሜ. በ7ሜትር) ፕሮጄክት መሃንዲስ

 14) ከጥር 1977 – መስከረም 1978 ዓ.ም.

 15) መስከረም 1975 - ታህሳስ 1976 ዓ.ም.

በኢመባ ተለማማጅ መሃንዲስ በመሆን በተለያዩ መምሪያዎችና ፕሮጄክቶች ላይ ሥልጠና ተሰጥቶታል እነዚህም

         መምሪያዎች 

  1.   የመንገድ ዲዛይን
  2.   የድልድይዲዛይን
  3.   የማቴሪያል ፍተሻ ቤተ ሙከራ

       ) ፕሮጄክቶች

  1. የቴፒ ጎሬ የጠጠር መንገድ ፕሮጄክት
  2. የዋቻ ማጂ የጠጠር መንገድ ፕሮጄክት
  3. ጎሬ ጋምቤላ የጠጠር መንገድ ፕሮጄክት
  4. ሻሸመኔ ሶዶ አስፋልት መንገድ ፕሮጄክት
  5. የአዋሽ ናዝሬት የአስፋልት ኦቨርሌይ ፕሮጄክት

           ) የማሰልጠኛ ጣቢያዎች

  1. የዓለም ገና የኢመባ ማስልጠኛ ማዕከል ስለ አስተዳደር ጉዳዮች ፣ ስለማናጅሜንት ፣ስለ ዋናመንገድ ና ስለ ግንባታ መሳሪያዎች መሰረታዊ ዕውቀት ሥልጠና ተሰጥተዋል
  2. የጊንጪ የዒመባ ማሰልጠኛ ጣቢያ በጉልበት ሰራተኞች ብቻ ሊሠራ ስለሚችል የገጠር መንገድ ግንባታ ቴክኒክ በንድፈ ሃሳብና በተግባር ስልጠና ወስዱዋል

ሠ)  ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ ያገኛቸው ሽልማቶችና የምስክር ወረቀቶች

  1. በኢትዮጵ አሠሪዎች ፌዴሬሽን የአማራ ክልል አጠቃላይ አሠሪዎች ማህበር ፤ የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን የዳይሬክተሮች የቦርድ አባልና የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ሃላፊ በመሆን ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተበረከተ የምስጋና የምስክር ወረቀት ታኅሣሥ 5 ቀን 2009 ዓ.ም.
  2. በባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ፤ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ ምክንያት ከነበረበት አደባባይ አንስቶ የባቡሩ መስመር ከተዘረጋ በሁዋላ ሃውልቱን ሥፍራው እንዲመለስ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣንንና ሌሎች አካላትን በማስተባበር ለተወጡት የአመራር የማይተካ ሚና የተበረከተ የምስክር ወረቀት ጥር 29 ቀን 2008 ዓ.ም.
  3. የወረጃርሶ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ላበረከቱት የመመሪያ አጋዥ መጽሃፍት እርዳታ መጋቢት 18 ቀን 2008 ዓ.ም የተበረከተ ምስክር ወረቀት
  4. መተባበር የልማት፣የጽዳት፣ የጥበቃና የመረዳጃ ዕድር የልማት ጥረቶቹን በማገዝ ላደረጉት አስተዋጽኦ መስከረም 17 ቀን 2008 ዓ.ም.የተበረከተ ምስክር ወረቀት
  5. በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረገ የከተሞች የመንገድ ልማት ውድድር አዘርዌይ በተሰኘ ዓለማዊ ተቐም በመመረጥ የአዲስ አበባ ከተሞች ባለሥልጣን የፕላቲኒየም ሽልማት በጣሊያን ሮማ ከተማ በመገኘት ሐምሌ 2007 ዓ.ም. በክብር ተቀብለዋል
  6. በኢትዮጵያ ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን አቅራቢነት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ፤ ለጥሩ አሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ሥራ አሥኪያጅነታቸው ላበረከቱት አስተዋጽዖ የተበረከተ የዋንጫ ሽልማት ጥቅምት 2007 ዓ.ም.
  7. የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአቶ መኩሪያ ሃይሌ በተማ ሥራዎች ዋና ዋና አጀንዳዎች ዙሪያ በተዘጋጁ ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች ላይ ከመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ጋር በመሆን በ 2 ዙር ለተካሄደ የከተማና ማዘጋጃቤታዊ አመራሮች ሥልጠና ላበረከቱት አዎንታዊ አስተዋጽ የተበረከተ የምስጋና ወረቀት ታኅሣሥ 22 ቀን 2007 ዓ.ም.
  8. በወረዳ 10 የአንቆርጫ ዳንሴ አካባቢ የዕድሮች ለልማት ጥምር ኮሚቴ ፤በመንገድ ለውጥ የህብረተሰብን ትርታ በማዳመጥ በአካባቢያችን የተከናወነ የድልድይና የመንገድ ሥራ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የተበረከተ የምስክር ወረቀት ጥር 2007 ዓ.ም.
  9. ጽርሀ ንግሥት ቅድሰት ሐና ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ፤የሃና ማሪያም የቀለበት መንገድ ድልድይ ሀና ማሪያም ቤተ ክርስቲያንን መንገድ ግንባታ በማስተባበር ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የተበረከተ የዕመቤታችን ቅድስት ማሪም ፎቶ ግራፍ ጥር 16 ቀን 2007 ዓ.ም.
  10.  የእንጦጦ ደብረ ሃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤሊያስ ቤተ ክርስቲያን ጽ/ቤት ፤ከእንጦጦ ደብረ ሃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤሊያስ ቤተ ክርስቲያን እስከ እንጦጦ ኬላ የተገነባውን የ 3.5 ኪ.ሜትር የአስፋልት መንገድ በማስገንባትና በማስተባበር ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተበረከተ የመልካም ሥራ ውጤት የምስክር ወረቀት ግንቦት 8 ቀን 2007 ዓ.ም.
  11. የአዲስ አበባ ከተማን የመንገድ አውታር በማስፋትና የፍሳሽ መሄጃ ፉካዎችን በማስገንባት ጤነኛ ህብረተሰብ እንዲፈጠር ላደረጉት አስተዋጽኦ ከመርካቶ አዲስ ከተማ አካባቢ ዕድር ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም የተበረከተ የተሳትፎ ምስክር ወረቀት
  12. የወጣቶችና ስፖርት ሚኒሰትር በአቶ ሬድዋን ሁሴን ለ12ኛው ታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር መሳካት የአዲስ አበባ እስታዲዮምን ዙሪያ አስፋልት በማልበስ ላደረጉት አስተዋጽኦ መጋቢት 2007 ዓ.ም የተበረከተ የምስክር ወረቀት
  13. በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የሠራተኛ ማህበር ማህበሩን በመደገፍ ከ1996 – 2006 ዓ.ም. ላበረከቱት አስተዋጽኦ የካቲት 2006 ዓ.ም የተበረከተ የምስጋና ምስክር ወረቀት
  14. በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 15 የመንገድ ልማት ኮሚቴ በወረዳው ለተከናወነው የመንገድ ልማት ልዩ አስተዋጽኦ በነዋሪው ስም ሐምሌ 2007 ዓ.ም. የተበረከተ ምስክር ወረቀት
  15.  የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፣ የፌዴሬሽኑን ቅድመ ምሥረታ 62ኛ ዓመትና 18ኛ ዓመት ዳግም ምሥረታን ምክንያት በማድረግ ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የተደረገውን ጉብኝት ከባለሃብቱ ጋር በማድረግዎ የተሰጠ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ሚያዝያ 27 ቀን 2007 ዓ.ም.
  16. ከታዋቂው ብስክሌተኛ ገረመው ደንቦባ የተበረከተ የሚከተውን ቃል የያዘ ካርድ “  ለተከበሩ ኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ዋና ሥራ አሥኪያጅ፤ እኔ ለእርስዎ የምመኝልዎ ቸሩ ፈጣሪ ከነ ቤተሰብዎ መልካም ጠየንነትና እረዥም ዕድሜ እንዲሰጥዎ ነው ፡፡ የተከበሩ ኢነጂ ፈቃደ ሺ አውል ማለት በተግባር እርስዎ መሆንዎ ከእግዚአብሄር የተሰጠዎ ጸጋ ነው ፤ለኢትዮጵያ ዕድገት ጸሎቴ ይኑሩልን ነው የምለው ፤ አክባሪዎና ከልብ የምወድዎ ገረመው ደንቦባ “
  17. በአራዳ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 8 የመንገድ ልማት ኮሚቴ በወረዳው ለተከናወነው የመንገድ ልማት ልዩ አስተዋጽኦ በነዋሪው ስም ኅዳር 13 ቀን  2005 ዓ.ም. የተበረከተ የምስጋና ምስክር ወረቀት
  18. ከለአለ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ርዕሱ ክረምት የተሰኘ መጠኑ 74 x 115 ሳ.ሜትር የሆነ በአበበ ተስፋዬ በ1991 ዓ.ም. የተሠራ የቀለም ቅብ ስዕል ለትምርት ቤቱ ላበረከቱት አስተውጽኦ የመምህራኑ ጉባዔ በወሰነው መሰረት መጋቢት 14 ቀን 2004 ዓ.ም. የህ የምስክር ወረቀትና ሥጦታው ተበረከተ
  19. የከቲት 11 ቀን 2004 ዓ.ም የህውሃት የምስረታ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ቢሮዎች ሲከበር በዓሉ በተሳካ ሁኔታ እነዲከበር ላደረጉት አስተዋጽኦ የተሰጠ የምስጋና ምስክር ወረቀት
  20.  በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሰፈረ ገነት የልማት ጣቢያ ነዋሪዎች ፡የመንገድ ጥያቄአችን ተመልሶልናል እናመሰግናለን የሚል የኢንጂነር ፍቃዱ ሃይሌን፤ የገተራ ማሳለጫንና የማዘጋጃቤትን ፎቶ ግራፍ የያዘ ትልቅ የፎቶ መታሰያ ግንቦት 2004 ዓ.ም.
  21. በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 6 መንደር 6 የመንገድ ልማት ኮሚቴ በወረዳው ለተከናወነው የመንገድ ልማት ልዩ አስተዋጽኦ በነዋሪው ስም ሰኔ 2003 ዓ.ም. የተበረከተ ምስክር ወረቀት
  22. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማናጅሜንት ዲፓርትሜንት፤ ለዲፓርትመንቱ የቢኤስሲ ተመራቂዎች በቴሲስ አድቫይዘርነት ላደረጉት አስተዋጽዖ የተሰጠ የአድናቆት የምስክር ወረቀት ሐምሌ 3 ቀን 2001ዓ.ም.
  23. የኪዳነ ምህረት ት/ቤት ት/ቤቱን በወላጅ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበርነት በማገልገል በትምህርቱ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በት/ቤቱ የተሰጠ የአድናቆት የምስክር ወረቀት ግንቦት 2001 ዓ.ም.
  24. ከኬሚካል ኮርፖሬሽን እስከ ቦሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተሠራውን መንገድ ምክንያት በማድረግ ለህብረሰተቡ ላበረከቱት ቅን አገልግሎት የቦሌ ክፍለ ከተማ 03/05፣04/05 እና የ07 ነዋሪዎች ያበረከቱት የምስጋና የምስክር ወረቀት ግንቦት 20 ቀን 2001 ዓ.ም.
  25. ሰላም ሰፈር ለምለም የጸጥታና የልማት ህብረት ባካሄደው የድልድይ ግንባታ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በእድሮቹ ህብረት ቦርድ ስምምነት የተበረከተ የምስክር ወረቀት የካቲት 7 ቀን 2001 ዓ.ም.
  26. የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፣እንጨት፣ብረታ ብረት ሲሚንቶና የመሳሰሉት ሠራተኛ ማህበራት ኢንደስትሪ ፌዴሬሽን በ15ኛ ዓመት ክብረበዓሉ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣንን በዋና ሥራ አሥኪያጅነት ሲመሩ የአሠሪና የሰራተኛውን ግንኙነት በፌዴሬሽናችን ውስጥ አርአያ ሊሆን የሚችል ያመራር ችሎታዎ ባለሥልጣን መሥሪያቤቱን ውጤታማ በማድረጉ በሰራተኛው ስም ያበረከቱት የምስክር ወረቀትና ፎቶግራፍ ጥር 30 ቀን 2001 ዓ.ም.
  27. የደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲታነጽ ላበረከቱት መንፈሳዊ አስተዋጽዖ የተበረከተ የላቀ የምስጋና ምስክር ወረቀት ህዳር 14 ቀን 2001 ዓ.ም.
  28.  ከአሜሪካን ሶሳይቲ ኦፍ ሲቪል ኢንጂነርስ በቦርድ ውሳኔ፤ የማህበሩ አባል ሆነው የተመረጡበት ሰርተፊኬት ሚያዚያ 2000 ዓ.ም.
  29. ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ባለፉት አሥር ዓመታት (ከ1990 – 2000ዓ.ም.) ባከናወነው የመንገድ ልማት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽዖ የተሰጠ የምሰክር ወረቀት  ሐምሌ 2000 ዓ.ም.
  30. ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮ ፤ የኢመባ የመጀመሪያው የመንገድ ልማት ፕሮግራምን (RSDP I) በማስተባበር (ከ1987 – 1995ዓ.ም.) ለተገኘው የመንገድ አውታር መሻሻል ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የተበረከተ የአድናቆት የምስክር ወረቀት ሰኔ 2000 ዓ.ም.
  31. በኮልፌ ቀራንዮ ቀበሌ 04 ቀጠና 7 ስልጤ ሰፈር ለተከናወነው የመንገድ ልማት ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላከናወኑት ከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነት በነዋሪው ስም ጥር 2000 ዓ.ም. የተበረከተ ምስክር ወረቀት
  32. በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 02 የደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ በጠጠር ልባስ እንዲሰራ ላደረጉልን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተበረከተ የላቀ የምስጋና ምስክር ወረቀት ታኅሣሥ 18 ቀን 2000 ዓ.ም.
  33. የቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 የአፓርታም አካባቢ የልማት ኮሚቴ ከ1994 አስከ 1999 ዓ.ም. በተካሄደው ከፍተኛ የመንገድ ልማት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተሰጠ ምስክር ወረቀት ነሐሴ 26 ቀን 1999 ዓ.ም.
  34. ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጠን የሰራተኛ ማህበር የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ የባለሥልጣኑን ዓመታዊ ሰፋፊ ዕቅዶች በማቀድና የአሠሪውንና ሠራተኛውን ግንኙነት በሰላማዊ ሁኔታ በመምራት ለውጤት በማብቃት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጥዖ የተሰጠ የመልካም አስተዳደር ምስክር ወረቀት ሐምሌ 14 ቀን 1999 ዓ.ም
  35. የሙራድ አምባ ሁለገብ ልማትና ተራድዖ ድርጅት ባሠራው የድልድይና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ ላበረከቱት ጉልህ ተሳትፎ የተሰጠ የከፍተኛ አስተዋጽዖ የምስክር ወረቀት ሐምሌ 1 ቀን 1999 ዓ.ም.
  36. ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና ማናጅሜንት ዲፓርትሜንት፤ ለመጀመሪያዎቹ የዲፓርትመንቱ የቢኤስሲ ተመራቂዎች በቴሲስ አድቫይዘርነት ላደረጉት አስተዋጽዖ የተሰጠ የአድናቆት የምስክር ወረቀት ነሐሴ 1998 ዓ.ም.
  37. የቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03/05 የ17-!7 ቁጥር 3 አካባቢ የልማት ኮሚቴ ከባለሥልጣኑ ጋር ላስገነባው የአስፋልትና የፍሳሽ ፕሮጄክት ላበረከቱት የላቀና ከፍተኛ አስተዋጽዖ በነዋሪውና በወረዳው የተሰጠ ለከፍተኛና ለላቀ ተግባር ምስክር ወረቀት ጥቅምት 1998 ዓ.ም.
  38. ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አርከበ ዑቁባይ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ መቃናት ላረከቱት አስተዋጽዖ የተሰጠ የምሰክር ወረቀት መስከረም 1998 ዓ.ም.
  39. የኪዳነ ምህረት ት/ቤት ት/ቤቱን በወላጅ ኮሚቴ አባልነት በማገልገል በትምህርቱ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በት/ቤቱ የተሰጠ የአድናቆት የምስክር ወረቀት ታኅሣሥ 2007 ዓ.ም.
  40. የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ባዘጋጀው ለገቢ ማሰባሰቢያ ዓላማ ሚያዝያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም. የእግር ጉዞ ተሳታፊ በመሆን ላሳዩት የድጋፍ ተሳትፎ እንርዳ ይርዱን የምስክር ወረቀት
  41. የዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል እድሳትና ግንባታ ማህበር ከአአ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ባደረገው የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ሚዝያ 20 ቀን 1997 ዓ.ም.
  42. ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አርከበ ዑቁባይ የዑራኤል ቦሌ መድሃኒዓለም ብራስ መንገድ ግንባታ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የተሰጠ የምሰክር ወረቀት የካቲት 27 ቀን 1997 ዓ.ም.
  43. ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አርከበ ዑቁባይ የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ ክፍል 1 እ 2 ግንባታን አስጀምሮ በማጠናቀቅ የአአ መንገዶች ባለሥልጣንን በመምራት ላደረጉት ከፍተኛ ተሳትፎ የተሰጠ የመልካም አስተዋጽዖ የምሰክር ወረቀት ሰኔ 1996 ዓ.ም.
  44. የኮተቤና ጉረድ ሾላ አጠቃላይ እድር፤ ዕድሩን በመምራት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የተሰጠ የመልካም አገልግሎት የምስክር ወቀት ነሐሴ 23ቀን 1996 ዓ.ም.
  45. ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አርከበ ዑቁባይ የኢትዮ ቻይናን የወዳጅነት ጎዳናን ግንባታን አስጀምሮ በማጠናቀቅ የአአ መንገዶች ባለሥልጣንን በመምራት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የተሰጠ የመልካም አስተዋጽዖ የምሰክር ወረቀት ታኅሣሥ 1996 ዓ.ም.
  46.  በወጣትነት ዕድሜው የ12ኛ ክፍለ ተማሪ በነበረበት ወቅት በመሰረተ ትምህርት የማስተማር ሂደትበ1971 ዓ.ም. በተካሄደው የመሰረተ ትምህርት ዘመቻ ተካፋይ በመሆን በጣቢያ ሃላፊነት በማገልገላቸው የተሰጠ የምስክር ወረቀት ሕዳር 1 ቀን 1972 ዓ.ም.
  47. በ1ኛ የደርጉ ተቀዳሚ ም/ል ሊቀመንበር ሻለቃ መንግሥቱ ሃይለማሪያም  ከኅብረተሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የዕድገት በህብረትየዕውቀትና የሥራ ዘመቻ ጠቅላይ መምሪያ ፤ የእናት አገር ጥሪን በማክበር ከ1967 – 1968 ዓ.ም. ድረስ በመዝመት ግዳጁን በመፈጸሙ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ሐምሌ 1 ቀን 1968 ዓ.ም.