ስርዓተ ቀብር

የዶ/ር ዮሴፍ ብሩ የቀብር ሥነ-ስርዓት 13/12/13 ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ከቀትር በኋላ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የስራ ባልደረቦቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡ 
ዶክተር ዮሴፍ ብሩ በተወለዱ በ52 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን በህይወት ዘመናቸው በርካታ ስራዎችን ለሀገራቸው ሰርተው ያለፉ ውድ የሀገር ባለውለታ ሲሆኑ በሲቪል ምህንድስና መስክ በተለያየ ሙያና ሀላፊነት ሀገራቸውን እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ከ25 ዓመታት በላይ በቅንነት አገልግለዋል፡፡ ኢንዱስትሪው በሀገሪቷ ኢኮኖሚ ውስጥ የላቀ ሚና መጫወት እንዲችል ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረትም አድርገዋል፡፡ በአገልግሎት ዘመናቸውም፡-

  • በኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር በቢሮ ኃላፊነት፤
  • በኢትዮጵያ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከመሥራችነት እስከ ዋና ዳይሬክተርነት፣
  • በአያት መኖሪያ ቤቶች ድርጅት በዋና ሥራ አስኪያጅነት፤
  • በጊፍት የመኖሪያ ቤቶች ድርጅት በዋና ሥራ አስኪያጅነት፤
  • በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን በቦርድ አባልነት፤
  • በተለያዩ የሀገሪቷ ዩኒቨርሲቲዎች በሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢነት እና አባልነት፤
  • በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተጋባዥ መምህርነት እና በምርምር ሥራ አማካሪነት፣
  • በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በቦርድ አባልነት፣
  • በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በአማካሪነት አገልግለዋል።

ዶ/ር ዮሴፍ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ከሀምሌ 28/ 2013 ዓ ም ጀመሮ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሲረዱ ቆይተው ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ ም አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው ነሀሴ 13/2013 ዓ.ም ተፈጽሟል፡፡ ዶ/ር ዮሴፍ ብሩ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ። በዶ/ር ዮሴፍ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛሉ፡፡