የሀዘን መግለጫ

የማህበራችን አባል የሆኑት ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ተክለ (Fellow Engineer) ከዚህ አለም በሞት መለየት ማህበሩ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸን
 በማህበራችን ከ1990 ዓ.ም  ጀምሮ ማህበሩን በመመስረትና ከመደበኛ አባልነት እስከ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ በመሆኑ ያገለገሉ ሲሆን ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ማህበሩን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በዕውቀትና በገንዘብ ሲደግፉ የቆዩ ሲሆን የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበርም የተሰማውን ልባዊ ሐዘን እየገለፀ  የቀብር ስነስርዓት ላይ  በሚደረገው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የማህበሩ አባላት በመገኘት ሐዘናችሁን እንድትገልፁ እናሳውቃለን፡፡   
በታማኝነት እና በስነምግባር  በሞያቸው አገራቸው ሲያገለግሉ የነበሩ መሆናቸውን ማህበሩ ይመሰክራል::
የኢትዮጵያ ሲቪል መሐንዲሶች ማህበር
#Condolence
On behalf of the Ethiopian Association of Civil Engineers, we want to express our deepest and most sincere condolences to the family and friends of Eng.Taddese HaileSilase (Fellow engineer) and EACE Community.
May his soul Rest in Peace
Ethiopian Association of Civil Engineers

የኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ተክለ አጭር
የህይወት ታሪክ

የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ/ም
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ተክለ ከእናታቸው ከወ/ሮ እልፍነሽ ወልደመድህን እና ከአባታቸው ከአቶ ኃ/ሥላሴ ተክለ በቀድሞ አርሲ ክ/ሀገር ዶዶታ ወረዳ ሊጋባ ከተማ ጥቅምት 14 ቀን 1933 ዓ/ም ተወለዱ፡፡
እደሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በአካባቢው ት/ቤት ትምህርት በመከታተል ላይ እያሉ፤ በ1940 ዓ/ም ክቡር ትዕዛዝ ወልደ ጊዩርጊስ ወልደ ዮሐንስ ወደ አዲስ አበባ አምጥተው በተፈሪ መኮንን ት/ቤት አስገብተው እየከፈሉላቸው እንዲማሩ አድርገዋል፡፡ እዚያው ት/ቤት አዳሪ በመሆን እስከ 12 ክፍል ድረስ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
በመቀጠል በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በ1953 ዓ/ም የምህድስና ኮሌጅ በመግባት በ1957 ዓ/ም ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል፡፡ በት/ቤት በነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በነበራቸው የአገር ፍቅር የተነሳ በወቅቱ በነበረው ""ተምሮ ማስተማር" በሚባል ፕሮግራም ቀዳሚ ተሳታፊ ነበሩ፡፡  
ከቀኃሥ ዩኒቨርስቲ እንደተመረቁ፣ ልምድ ለማግኘት በቀን ሙያተኛነት በመቀጠር፤ አሁን ዋናው ፖስታ ቤት ያለበት ህንጻ በሚገነባበት ጊዜ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ላይ እየታዩ ደረጃ በደረጃ እስከ ፕሮጀክቱ ዋና መሐንዲስነት ድረስ አገልግለዋል፡፡
በመቀጠል  ታደሰ ኃ/ሥላሴ  ኮንስትራክሽን በሚል የራሳቸውን አቋቁመው ነበር፡፡  ድርጅቱን በማሳደግ ከኢንጂኔር ብርሃነ አባተ ጋር በመሆን በርታ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበርን አቋቋመዋል፡፡ አገር በቀል የሆኑ ተቋራጮች ሲመሠረቱ ከቀደምቶቹ አንዱ በመሆን፤ በርታ ኮንስትራክሽን በተለያዩ የመንገድ ሥራዎች ለምሳሌ ፡- ብቸና ሞጣ፣ ጅማ ጭዳ፣ ሰርዶ አፍዴራ፣ ጋሸና ላሊበላን ገንብተዋል፡፡  ፋብሪካም ገንብተዋል ለምሳሌ፡- የሐረር ቢራ ፋብሪካ፣ ሜታ ቢራ ፋብሪካ፣  ለቱሪስት መዳረሻ የሚሆኑ ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ በባህር ዳር "ጣና ሐይቅ" በጎንደር "ጎሃ" በላሊበላ "ሮሃ" በአክሱም "የሃን" በሒልተን ሆቴል ደረጃ የሆኑ አራት ሆቴሎችን ገንብተዋል፡፡ በሰፋፊ የመስኖ ሥራ ተግባራትም ተሳትፈዋል፣ለምሳሌ የአሚባራ መስኖ ፕሮጀክት፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃሥላሴ ስለ አገር ልማት የነበራቸው ህልም ከፍ ያለ ነበር፡፡ በተለያዩ መድረኮች ለአገር ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ ሃሳቦችን አቅርበዋል፤ ያገባኛል የሚሉ ወገኖችም በሃሳባቸው ዙሪያ እንዲወያዩ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪ ኢንጂነር ታደሰ ኃሥላሴ ስለ አገር ልማት ጽሑፎችን ለሕዝብ በተደጋጋሚ አበርክተዋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ ጥረት በህዝብ ሚዲዎች ብዙ ገለጣዎችን አከናውነዋል፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ያቀርቧቸው የነበራቸው የልማት አስተያየቶች ላይ ተመርኩዞ በ2011 ዓ/ም በተመሠረተ የመሐንዲሶች የጥናት ቡድን፡ በ2050 ኢትዮጵያ በልማት የት ልትደርስ ትችላለች በሚል በተዘጋጀ መድረክ እውቅና ተሰጥቷቸው ተሸልመዋል፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ስላሴ በጣም ግልጥና  በጣም ቅን ግለሰብ ነበሩ፡፡ እሳቸውን መሰል ቅን ሰው ማግኘት ያዳግታል፡፡ ኢንጂነር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ሚያዝያ 1967 ዓ/ም ከወ/ሮ ሂሩት አማረ ጋር ትዳር መሥርተው ለ46 ዓመት እስከ እለተሞታቸው ድረስ በፍቅር አብረው ኖረዋል፡፡
ኢንጂኔር ታደሰ ኃ/ሥላሴ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ80 ዓመታቸው የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ/ም በሞት ተለይተውናል፡፡ ቀብራቸው  የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ/ም በአራዳ መናገሻ ቅዱስ ጊዩርጊስ ቤተ ከርስቲያን ይፈፀማል ፡፡